Feb. 24, 2025 | Categories:
News
ሰበታ አግሮ ኢንዱስትሪ ከኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት የብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ተበረከተለት
ሰበታ አግሮ ኢንዱስትሪ በብራንድ ስሙ የሚታወቀው ማማ ወተት ከኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት የብቃት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት ተረከበ።
የሰበታ አግሮ ኢንደስትሪ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሳራ ሀሰን ሰበታ አግሮ ኢንዱስትሪ ለምግብ ደህንነት እና ጥራት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት አለማቀፍ የምግብ ደህንነት ስርዓት ISO 22000:2018 Food safety Management system እና አለማቀፍ የጥራት ስራ አመራር ስርዓት ISO 9001:2015 Quality Management system ሰርቲፋይድ መሆኑን የገለፁ ሲሆን አክለውም ሰርተፍኬቱ ለቀጣይ ስኬት አነሳሽ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡